Friday, 2024-05-03, 10:43 AM
ETHIOPIAN POLITICS current event and news
Main Registration Login
Welcome, Guest · RSS
Site menu
    news
    news
    curency
    Calendar
    «  October 2011  »
    SuMoTuWeThFrSa
          1
    2345678
    9101112131415
    16171819202122
    23242526272829
    3031
    Site friends
     
    Main » 2011 » October » 7 » ፍኖት - ልጄ በረሃብ ሞተብኝ! ወ/ሮ አስናቀች October 7th, 2011
    10:45 PM
    ፍኖት - ልጄ በረሃብ ሞተብኝ! ወ/ሮ አስናቀች October 7th, 2011

    የደረሰብኝን በደል ለመንግስት አሳውቁልኝ ሲሉ ወ/ሮ አስናቀች ገ/መድህን ዝግጅት ክፍላችንን ተማፀኑ፡፡ በአዲስ ከተማ ክ/ከ ወረዳ 7 (በቀድሞ ቀበሌ 16/17) የቤት ቁጥር 750/2 ነዋሪ የሆኑት የቤት እመቤት እምባቸውን እያረገፉ ሁለት የወረዳው ባለሥልጣናት በህጋዊ መንገድ የተሰጠኝን ማብሰያ አፍርሰው ዕቃዬን ውጪ ስለወረወሩብኝ ልጆቼን አብስዬ የማበላበት ቦታ አጥቼ በመቸገሬ ትንሹ ልጄም በረሃብ ሞተብኝ” ሲሉ በማያቋርጥ ለቅሶ ዝግጅት ክፍላችን በመገኘት አንብተዋል፡፡

    ወ/ሮ አስናቀች እንደሚሉት "እኔ ከቫይረሱ ጋር የምኖር ዜጋ ነኝ” ካሉ በኃላ በመቀጠል "ለአዲስ አበባ ከተማ የባለ አደራ መስተዳድር ከንቲባ ብርሃኑ ዱሪሳ አመልክቼ የተሰጠኝ ማብሰያ ቤት የወረዳው መስተዳድሮች ፍጹም ሰብአዊነት በጐደለው ሁኔታ ቤቱን አፈራርሰው ዕቃዬን ሜዳ ላይ ወረወሩት፡፡

    አምስት ልጆች አሉኝ፡፡ ከአምስቱ አንዱ በረሃብ ሞተብኝ፡፡ መንግስት መድኃኒት በነፃ ይሰጠናል፡፡ ህብረተሰቡ እህል እየሸመተ ያቀርብልናል፡፡ 50 ኪ.ግ የተፈጨ እህል እያለኝ ማብሰያ ቦታ አጥቼ ልጄን አጣሁ፡፡ መንግስት ምንም አልበደለኝም፡፡ በወረዳ እና በቀበሌ ያሉት ግን ሊያስቀምጡን ሊያኖሩን አልቻሉም፡፡ ሰውን እንደሰው አያዩም፡፡ትቢታቸውና እብሪታቸው ያሳዝናል፡፡ መንግስት የሚያስቀምጣቸውን ሰዎች በትክክል አያውቅቸውም፡፡ ህዝብን በአግባቡ አገልግሎት እየሰጡ አይደለም መንግስት ይወቅልን ጩኸቴን ለመንግስት አሰሙልኝ” ሲሉ ብሶታቸውን በመሪሪ ሐዘን ገልፀዋል፡፡

    ሕወሃት ኢሕአዴግ ኢቲቪን፣ ራዲዮዉን በሙሉ ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ አፍኖ ይዟል። የአንድነት ፓርቲ በፍኖት ጋዜጣ ሕዝቡን ለመድረስ፣ ለማስተማር እየሞከረ ነዉ። ጋዜጣዉን በብዛት ለማሳተም፣ በአገሪቷ ክፍሎች በስፋት ለማሰራጨት የገንዘብ አቅም ይጠይቃል።፡ለዚህ ኢትዮጵያዊ አላማ የድርሻዎትን ይወጡ ዘንድ አገራዊ ጥሪ እናቀርባለን። በገንዘብዎት አገር ቤት የሚደረገዉን ትግል ይርዱ።
    የፍኖት እትም አሥር ሙሉዉን ለማንበብ ከዚህ ይጫኑ

    Views: 700 | Added by: dani | Rating: 4.0/1
    Total comments: 0
    Name *:
    Email *:
    Code *:
    Copyright MyCorp © 2024
    Create a free website with uCoz