Saturday, 2024-05-04, 8:57 PM
ETHIOPIAN POLITICS current event and news
Main Registration Login
Welcome, Guest · RSS
Site menu
    news
    news
    curency
    Calendar
    «  October 2011  »
    SuMoTuWeThFrSa
          1
    2345678
    9101112131415
    16171819202122
    23242526272829
    3031
    Site friends
     
    Main » 2011 » October » 28 » ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች በድጋሚ በትላንትናው ዕለት ፍ/ቤት ቀረቡ October 27th, 2011
    7:36 PM
    ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች በድጋሚ በትላንትናው ዕለት ፍ/ቤት ቀረቡ October 27th, 2011

    "በሽብር” ተግባር ተጠርጥረው ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ከሚገኙት እስረኞች መካከል የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ /ኢብአፓ/ ፕሬዝደንት አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔር፣ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ፣ጋዜጠኛ ርዕዮትዓለሙና ወ/ሮ ሂሩት ክፍሌ በትላንትናው ዕለት ፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል፡፡ መዝገቡ ተቀጥሮ የነበረው በክስ አቀራረቡ ላይ የተከሳሽ ጠበቆች ባቀረቡት ተቃውሞ ክሱ እንዲሻሻል ፍ/ቤቱ ብይን በመስጠቱ ነው፡፡ ተሻሽሎ በቀረበውም ክስ በተመሳሳይ ሁኔታ ጠበቆች ቅሬታ በማቅረባቸው ለሁለተኛ ጊዜ በድጋሚ ለብይን ለዛሬ ተቀጥሯል፡፡

    ቀደም ሲል ለትላንትናው ዕለት የተቀጠረው ጥቅምት 9 ቀን 2004 ዓ.ም በነበረው ቀጠሮ በዓቃቤ ህግ መ/ቁ 039/04 በፌዴራል ፖሊስ መ/ቁ 13459/03 በቀረበው የክስ ቻርጅ ላይ የተከሳሽ ጠበቆች ባቀረቡት
    የቅሬታ አቤቱታ ፍ/ቤቱ የዐቃቤ ሕጉን ምላሽ ካደመጠ በኂላ በተወሰኑ ነጥቦች ላይ ዐቃቤ ሕግ ክሱን አሻሽሎ
    ለጥቅምት 13/04 ዓ.ም እንዲቀርብ በተሰጠው ብይን መሠረት ነው፡፡ የአቶ ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔር የጋዜጠኛ
    ውብእሸት ታዬና የወ/ሮ ሂሩት ክፍሌ ጠበቃ የሆኑት ጠበቃ ደርበው ተመስገንና የመምህርትና ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ጠበቃ የሆኑት ጠበቃ ሞላ ዘገየ ለፍ/ቤቱ ባቀረቡት አቤቱታ "በደንበኞቻችን ላይ የቀረበው የክስ ቻርጅ የሽብር ተግባር ለመፈፀም በመስማማት ይላል፤የትና መቼ እንደተስማው አይገልጽም፡፡

    የሽብር ተግባር ለመፈፀም የሥራ ክፍፍል በማድረግ ይላል፤የእያንዳንዱ የሥራ ድርሻ አልተገለፀም፡፡ ገንዘብ ድጋፍ ጠያቄ ከአሸባሪ ቡድኑ በኤልያስ ክፈሌ በኩል በስውርና በረቂቅ መልኩ እየተደረገላቸው የሽብር ተግባርን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ይላል፤በምን የሽብር ተግባር ገንዘቡ አንደተገኘና ከየትኛው የሽብር ድርጅት ገንዘቡ እንደተገኘ አልገለፁም፡፡ የሽብር ተግባር ለመፈፀም እንዳደራጁ ሰው እንደመለመሉ ይገልጻል፡፡ ማንን እንዳዳራጁና እንደመለመሉ በግልጽ አልተገለፀም፡ ፡ ስለዚህ በግልጽ ባልተገለፀበት ሁኔታ ለመከላከል እንቸገራለን በማለት አቤቱታ አቅርበዋል፡፡ በተጨማሪ
    የክሱ ኤግዚቢትም አንደሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡

    ዐቃቤ ህግም የክሱ ወንጀል የተገለፀ ሲሆን ድርጊቱም በቂ በማስረጃ ይረጋገጣል በማለት መልስ የሰጠ ሲሆን ከተጠርጣሪዎች የተገኘ ኤግዚቢት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ለፍ/ቤት ማስረጃ ሆኖ ከመቅረብ ውጪ ለተከሳሽ የምንሰጥበት የሕግ አግባብ የለም በማለት መልስ ሰጥቷል፡፡ የግራና ቀኝ ክርክሩን ያዳመጠው ፍ/ቤትም በሰጠው ብይን "ቀኑ ቢጠቀስ ጥሩ ነበር፡፡ ባይጠቀስም ወደፊት በማስረጃ የሚታይ ይሆናል፡፡ ኤግዚቢት ለተከሳሽ መሰጠት አለበት ብለን
    አላመንበትም፡፡ ዐቃቤ ሕግ አመራሮቹንና ተመሪዎቹን በመለየት የተከሳሾቹን የሥራ ድርሻ በመለየት ክሱን
    አሻሽሎ ያቅርብ” ብሏል፡፡

    በተሻሻለው ክስ መሠረት በትላንትናው ዕለት የቀረቡት ተከሳሾች ሁለተኛ ተከሳሽ ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔርና 3ኛ ተከሳሽ ውብእሸት ታዬ በአመራር እና በውሳኔ ሰጪነት 4ኛ ተከሳሽ ወ/ሮ ሂሩት ክፍሌና 5ኛ ተከሳሽ ርዕዮት ዓለሙ በተባባሪነትና ሰው በመመልመል የወንጀል ተግባር ፈጽመዋል በሚል ተሻሽሏል፡፡ የ5ኛ ተከሳሽ ጠበቃ ሞላ ዘገየ እንዳመለከቱት በመጀመሪያው ክስ ደንበኛዬ ሰው መልምላለች አይልም አሁን እንዴት ሊጨመር ቻለ? አይደለም ክሱ ግልጽ አይደለም፡ በማለት ቅሬታ አቅርብዋል፡፡ ዐቃቤ ሕጉም ክሱን ያሻሻለበትን ሁኔታ አስረድቷል፡፡ ፍ/ቤቱ ብይን
    ለመስጠት ለዛሬ ጥቅምት 14 ቀን ተቀጥሯል፡፡

    Views: 582 | Added by: dani | Rating: 4.0/1
    Total comments: 0
    Name *:
    Email *:
    Code *:
    Copyright MyCorp © 2024
    Create a free website with uCoz