Monday, 2024-04-29, 10:01 PM
ETHIOPIAN POLITICS current event and news
Main Registration Login
Welcome, Guest · RSS
Site menu
    news
    news
    curency
    Calendar
    «  October 2011  »
    SuMoTuWeThFrSa
          1
    2345678
    9101112131415
    16171819202122
    23242526272829
    3031
    Site friends
     
    Main » 2011 » October » 18 » በኦታዋ-ካናዳ የኢትዮጵያኖች ቁጣ !Monday, October 17th, 2011
    8:11 PM
    በኦታዋ-ካናዳ የኢትዮጵያኖች ቁጣ !Monday, October 17th, 2011

    Click here for PDF

    ከሩቅ እያስገመገመ አካባቢውን የሚያናውጠው ድምፅ እየተቃረበ በመምጣቱ መሃል ኦታዋ መናጥ ጀምራለች ። ጡሩምባው ፣ ፊሽካው ፣ ፉጨቱ በህብረት ያስተጋባል ። ኢትዮጵያኖች በአንድነት ሆነው ቁጣቸውን እየገለጡ ናቸው ።

    ኦክቶበር 11፣ 2011 ከረፋዱ 11፡30 ጀምሮ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ዘር ሳይለይ በህብረት ተቃውሞውን ለመግለፅ በካናዳ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፊትለፊት ተሰብስቦ ብሶቱን ያሰማል ።

    -       መለስ ዜናዊ ቴረሪስት ነው !

    -       ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ !

    -       የህዝብ ልሳን የሆኑ ጋዜጠኞች በአስቸኳይ ይፈቱ !

    -       ካናዳ ለሽብርተኛው የመለስ ዜናዊ መንግስት የምታደርገውን እርዳታ ታቁም !

    Ethiopians in Ottawa, Canada demonstration 2011የመሳሰሉት የብሶት ድምፆች በአካባቢው ላይ በከፍተኛ ድምፅ ይስተጋባሉ ። የሃገራቸው የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል ፣ ፍትህና እኩልነት በዚያች አገር መስፈን አለበት ፣ ለሰብዓዊ መብት መጠበቅና በአገራችን ዲሞክራሲ መስፈን አለበት ብለው ቆርጠው በተነሱ ኢትዮጵያውያኖች ላይ የሚታየው እልህና ቁርጠኝነት ኢትዮጵያችን ዛሬም የወላድ መካን እንዳልሆነች ያረጋግጣል ።

    የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው ፕሮግራም ፣ የአዲስ ድምፅ ሬድዮ ፣  ከረንት አፌርስ ፣ ቃሌ የውይይት ክፍልና  ከፍተኛ ተደማጭነት ያላቸው መገናኛ ብዙሃን አንቴናቸውን ተክለው ከዚያው ከካናዳ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፊት ለፊት በቀጥታ የተቃውሞ ሰልፉን እየዘገቡ ነው ።

    የካናዳ ቴሌቪዥንና ሲቲኤን ጨምሮ የተለያዩ ሚዲያዎች በተቃውሞ ሰልፈኞቹ መካከል በመዘዋወር ቃለ መጠይቅ ያደርጋሉ ። ኢትዮጵያውያኖች ቆርጠዋል ። አረንጓዴ ቢጫና ቀይ ባንዲራችንን አንገቱ ላይ እንደ ማተብ ያላሰረና ከፍ አድርጐ የማያውለበልብ አንድም የአገር ተወላጅ አይታይም ።

    ኢትዮጵያውያኖች ልዩነታቸውን ወደ ጐን ማድረጋቸውንና የጋራ ጠላታቸውን በህብረት ለመፋለም መዘጋጀታቸውን በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል ። የኢትዮ-ካናዳውያን ፎረም ለዲሞክራሲ ስብስብ ለዚህ ያለአንዳች ልዩነት የእጅ ለእጅ የመያያዝ ህብረት ዋናው መሰረት ነው ። ይህ ስብስብ ወደፊትም በአገራችን የፖለቲካ መድረክ ጉልህ ሚና ይጫወታል ተብሎ ከፍተኛ ተስፋ ይጣልበታል ።

    ቀደም ብሎ ከውስጡ መርጦ ያዘጋጃቸው ሶስት አባላትን ያካተተ ቡድን የተቃውሞ ስብሰባውን ዓላማና በመለስ ዜናዊ መንግስት አማካኝነት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየተካሄደ ያለውን Demonstration in Ottawa, Canadaየከፋ ሽብርተኝነት የካናዳ መንግስትና ህዝብ እንዲያውቀው ለማስረዳትና የተዘጋጀውንም ደብዳቤ ለካናዳ መንግስት ተወካይ በእጅ ለመስጠት በመጠባበቅ ላይ ናቸው ።

    የኢትዮጵያውያን የብሶት ድምፅ አካባቢውን እያናወጠ ባለበት ሰዓት በካናዳ መንግስት የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ተወካይ በስሜት በመነካትና በከፍተኛ አክብሮት ሰላማዊ ሰልፈኝቹን በመወከል የቀረቡትን ሶስት አባላት ተቀብለው ካነጋገሩ በኋላ ለመንግስታቸው የተዘጋጀውን ደብዳቤ በመቀበል ፤ በተጨማሪም ከኢትዮጵያውያኖች ጋር በቀጣይ በጠረጴዛ ዙሪያ በመቀመጥ ስለ ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝና የዲሞክራሲን ግንባታ በተመለከተ ለመወያየት ቃል ገብተው በመጡበት አኳኋን ተመልሰዋል ።

    በኦታዋ በኢትዮ-ካናዳውያን የተካሄደው የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ የሽብርተኛውን የመለስ ዜናዊን መንግስት የሰብዓዊ መብት ጥሰት በማጋለጥ ደረጃ ግቡን መምታቱንና ኢትዮጵያውያኖችን በዘር ሳይከፋፍል ልዩነታቸውን ወደ ጐን በመተው በአንድነት እጅ ለእጅ ያስተሳሰረ እንደነበረ ከቦታው ሆነን ለመዘገብ ችለናል ።

    ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !

    በኦታዋ የኢትዮ-ካናዳውያን ፎረም ለዲሞክራሲ

    ኦክቶበር 12፣2011

    Views: 609 | Added by: dani | Rating: 4.0/1
    Total comments: 1
    1 brautkleider  
    0
    Sechsunddreißiger-Ausschusses: „Wir — er sprach also im Namen von
    dem namentlich die Frage nach einer zentralen Leitung für die
    bekam er eine zweite Portion.

    Name *:
    Email *:
    Code *:
    Copyright MyCorp © 2024
    Create a free website with uCoz