Sunday, 2024-05-05, 2:06 AM
ETHIOPIAN POLITICS current event and news
Main Registration Login
Welcome, Guest · RSS
Site menu
    news
    news
    curency
    Calendar
    «  December 2011  »
    SuMoTuWeThFrSa
        123
    45678910
    11121314151617
    18192021222324
    25262728293031
    Site friends
     
    Main » 2011 » December » 5 » አቡጊዳ – ይኼ ክስ በኢትዮጵያ የሚደረገውን ሰላማዊ ትግል ለማፈን የተዘጋጀ የውሸት ዲሪቶ ነው፤ – አንዱዋለም አራጌ December 4th, 2011
    7:24 PM
    አቡጊዳ – ይኼ ክስ በኢትዮጵያ የሚደረገውን ሰላማዊ ትግል ለማፈን የተዘጋጀ የውሸት ዲሪቶ ነው፤ – አንዱዋለም አራጌ December 4th, 2011

    በሽብር ተግባር ተሰማርታችኋል በሚል የፈጠራ ክስ የተከሰሱ፣ በአገር ቤት ሰላማዊ በሆነ መንገድ የኢትዮጵያ ሕዝብ መብቱና ነጻነቱ እንዲረጋገጥለት በመታገል የሚታወቁት የአንድነት ፓርቲ ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ አንዱዋለም አራጌ፣ እዉቁ ጋዜጠኛ አቶ እስክንድር ነጋ ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያዉያን የቀረበባቸዉን ክስ እንዲከላከሉ ፍርድ ቤቱ የወሰነ ሲሆን ፣ የቀረበባቸዉ ክስ መሰረት የሌለዉ እንደሆነ በመግለጽ ጥፋተኛ እንዳልሆኑ አረጋግጠዋል። በተለይም አቶ አንዳዋለም አርጌ «ጥፋተኛ ነህ ? » ለሚለዉ የፍርድ ቤት ጥያቄ "ይኼ ክስ በኢትዮጵያ የሚደረገውን ሰላማዊ ትግል ለማፈን የተዘጋጀ የውሸት ዲሪቶ ነው” በማለት ያጣጣለዉ ሲሆን ምንም አይነት አስተያየት ለመስጠት ፍቅደኛ እንዳልሆነም ሪፖተር ዛሬ ባወጣዉ እትሙ ዘግቧል።

    የሪፖርተርን ዘገባ ከዚህ በታች ለአንባብያን አቅርበናል፡

    ===============================
    ሪፖርተር

    ሪፖርተር የዘገበዉን በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው እነ አንዱዓለም አራጌ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ‹‹አኬልዳማ›› በሚል ያዘጋጀው ፕሮግራም የእኛንና የፍርድ ቤቱን ክብር ነክቷል፣ ስማችንንም አጉድፏል፤›› በማለት ኅዳር 20 ቀን 2004 ዓ.ም. ለፍርድ ቤቱ አመለከቱ፡፡ ፍርድ ቤቱ ‹‹ስለራሳችሁ መብት ብቻ ተናገሩ›› በማለት ምላሽ ሰጥቷል፡፡

    የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ክስ ከተመሠረተባቸው 24 ተከሳሾች መካከል፣ በችሎት ተገኝተው ክሳቸውን በመከታተል ላይ ያሉት ስምንት ተጠርጣሪዎች፣ ያቀረቡትን የክስ ይሻሻልልን ጥያቄ ተቀብሎ እንዲሻሻል ትዕዛዝ የሰጠበትን አንደኛና አራተኛ ክስ ለማየት፣ ኅዳር 20 ቀን 2004 ዓ.ም. የተሰየመው ከጠዋቱ 3፡45 ሰዓት ነበር፡፡

    ዓቃቤ ሕግ ክሱን አሻሽሎ ማቅረቡን ፍርድ ቤቱ ካረጋገጠ በኋላ አስተያየታቸውን የሰጡት የተከሳሾቹ ጠበቆች፣ አንደኛው ክስ ምንም እንዳልተሻሻለ በመጥቀስ በድጋሚ ዓቃቤ ሕግ ክሱን አሻሽሎ እንዲቀርብ ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው አመልክተው፣ በአራተኛው ክስ ላይ ግን ምንም ተቃውሞ እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡

    አንደኛው ክስ ባለሥልጣናት መግደል፣ ተቋማትን ማፈራረስ፣ የፋይንስ ተቋማትን መዝረፍ፣ ወዘተ የሚሉ ጭብጦችን የያዘ በመሆኑ፣ ማን ማንን ሊገድል እንዳሰበ፣ ማን የትኛውን ተቋም ሊያፈርስ እንዳቀደና ማን የትኛውን የፋይናንስ ተቋም ለመዝረፍ እንደተዘጋጀ በዝርዝር አለመገለጹን መጥቀስ፣ ዓቃቤ ሕግ በግልጽና በዝርዝር እንዲያስቀምጥላቸው ነበር የተከሳሾቹ ጥያቄ፡፡ ሆኖም ፍርድ ቤቱ እንዲሻሻል ትዕዛዝ የሰጠ ቢሆንም፣ ምንም አለመሻሻሉን ለፍርድ ቤቱ አመልክተው ድጋሚ ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው ጠየቁ፡፡

    ዓቃቤ ሕግ በሰጠው ምላሽ፣ ክሱን ሲመሠርት የጠቀሰው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 38(1) እና የፀረ ሽብርተኝነት አዋጁ አንቀጽ 4 የሚያስረዳው፣ ተጠርጣሪዎቹ ድርጊቱን ለመፈጸም ማሴራቸውን፣ ማደማቸውን፣ ግንቦት 7 ከሚባለው አሸባሪ ቡድን አመራሮች ባለሥልጣናትን እንዲገድሉ፣ ዜጎችን እንዲያፍኑ፣ ከፍተኛ የመንግሥት ተቋማትን እንዲያፈራርሱ፣ የገንዘብ ተቋማትን እንዲዘርፉና እንዲያዘርፉ ትዕዛዝ ተቀብለዋል፣ አባልና አመራር ሆነዋል እንጂ፣ በተናጠል ፈጽመዋል የሚል ክስ ስላልቀረበላቸው ጥያቄና ተቃውሞአቸው ውድቅ እንዲደረግለት ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡

    በተለይ በ2003 ዓ.ም. ሊፈጸም የነበረን ዓላማ ለማስፈጸም ሥራ ተከፋፍለው እንደነበር የሚያስረዳ ክስ በመሆኑ፣ ተነጣጥሎ መቅረብ የሌለበትን ክስ ማቅረቡንም ዓቃቤ ሕግ ለፍርድ ቤቱ አስታውቋል፡፡

    ፍርድ ቤቱ በሰጠው ብይን፣ ዓቃቤ ሕግ ባቀረበው ክስ ላይ በጠቀሰው የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 4 ሥር በዝርዝር የተጠቀሰ በመሆኑና እያንዳንዱ ተጠርጣሪ በተናጠል ፈጸመ ያለው ነገር እንደሌለ በመግለጽ፣ የተከሳሾቹን ተቃውሞ ውድቅ በማድረግ፣ ተከሳሾቹ የእምነት ክህደት ቃላቸውን እንዲሰጡ አዟል፡፡

    አንደኛ ተከሳሽ የሆነው የአንድነት ፓርቲ ቃል አቀባይ አንዱዓለም አራጌ ‹‹ድርጊቱን ፈጽመሀል አልፈጸምክም›› በሚል ከፍርድ ቤቱ ለቀረበለት ጥያቄ፣ ‹‹ይኼ ክስ በኢትዮጵያ የሚደረገውን ሰላማዊ ትግል ለማፈን የተዘጋጀ የውሸት ዲሪቶ ነው፤›› ሲል፣ ‹‹ፈጽሜያለሁ ወይም አልፈጸምኩም›› ማለት እንጂ ሌላ መናገር እንደማይችል ፍርድ ቤቱ ገልጾለት፣ በድጋሚ ሲጠይቀው ዝምታን በመምረጡ፣ ፍርድ ቤቱ ‹‹ድርጊቱን አልፈጸኩም›› ብለዋል በሚል እንዲመዘገብ አድርጓል፡፡

    ሁለተኛው ተከሳሽና የአንድነት ፓርቲ አመራር አባል የሆነው ናትናኤል መኮንንም ሲጠየቅ ‹‹በሰላማዊ መንገድ መታገሌ ወንጀል ከሆነ ፈጽሜያለሁ፤›› ብሏል፡፡ ሦስተኛና አራተኛ ተከሳሾች ዮሐንስ ተፈራና የሽዋስ ይሁንዓለም ‹‹በክስ ቻርጁ የተዘረዘረውን አልፈጸምንም፤›› በማለት የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡

    አምስተኛው ተከሳሽ ክንፈ ሚካኤል ደበበ ሲጠየቅ፣ ‹‹በክስ ቻርጁ የተዘረዘረውን ተረታ ተረቶች አልፈጸምኩም፤›› ሲል፣ ፍርድ ቤቱ ቆሞበት ከነበረበት ቦታ ወደፊት እንዲወጣ በማድረግ፣ ‹‹ፍርድ ቤቱ የሚያስከብረው ዜጐች ሲያከብሩት የኖሩትን የኢትዮጵያን የወንጀል ሕግ ነው፤ እንድታደርግ እየተጠየቅህ ያለው በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ ውስጥ ከተቀመጠው አንዱን አንቀጽ ነው፡፡ በተቀመጠው ሕግ መሠረት መግለጽ እንጂ፣ ሌላ ነገር መናገር የፍርድ ቤቱ ሥነ ሥርዓት አይደለም፡፡ የውስጥ ስሜታችሁን የምትገልጽቡት ቦታና ጊዜ አለው፤›› በማለት ካስጠነቀቀው በኋላ በድጋሚ ጠይቆት ‹‹አልፈጸምኩም›› ብሏል፡፡

    ስድስተኛ ተከሳሽ ምትኩ ዳምጤ፣ ሰባተኛ ተከሳሽ እስክንድር ነጋና ስምንተኛ ተከሳሽ አንዱዓለም አያሌው የእምነት ክህደት ቃላቸውን እንዲሰጡ ሲጠየቁ፣ ‹‹ድርጊቱን አልፈጸምንም፤ ጥፋተኛም አይደለንም፤›› ብለዋል፡፡

    ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ የሰጡትን የእምነት ክህደት ቃል ካደመጠ በኋላ ዓቃቤ ሕግ አስተያየት እንዲሰጥ ጠይቆ፣ ተከሳሾቹ የቀረበባቸውን ክስ የካዱ በመሆናቸው፣ ‹‹እንደ ክሳችን የሚያስረዱልንን የሰዎች ምስክሮች እንድናሰማ (35 ናቸው ብሏል) ተለዋጭ ቀጠሮ ይሰጠን፤›› ሲል፣ ተከሳሾቹ ከተቀመጡበት በመነሳት እጃቸውን አወጡ፡፡

    ፍርድ ቤቱ ‹‹አሁን ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠት እንጂ አቤቱታ አንቀበልም፤›› ሲል፣ ከተከሳሾች ጠበቆች አንዱ ‹‹ክቡር ፍርድ ቤት የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን የደንበኞቻችንን ስም እያጠፋ ነው፡፡ ይኸ ችሎት ሕጋዊ ችሎት ነው፤ ዕርምጃ ሊወስድ ይገባል፡፡ መብትን የተመለከቱ ነገሮች በጽሑፍ እንዲቀርቡ መደረግ የለበትም፤›› አሉ፡፡

    ‹‹ማመልከቻችሁን በጽሑፍ አቅርቡና የሚመለከተው አካል መልስ እንዲሰጥበት ይደረጋል፤›› በማለት ፍርድ ቤቱ ሲናገር፣ አንዱዓለም አራጌ በመሀል ተነስቶ፣ ‹‹እዚህ ፍርድ ቤት ተከስሼ ስቀርብ የመጀመርያዬ አይደለም፡፡ ይኼ ችሎት ግን ሊሰማን አልቻለም፡፡ በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን መብታችን እየተጣሰ፣ ስማችን እየጠፋ፣ ክብራችን እየተነካ፣ የፍርድ ቤቱም ነፃ ሆኖ የመዳኘት መብት እየተነካ ለምን በጽሑፍ አቅርቡ እንባላለን? ድራማ እየተሠራብን እኮ ነው፤›› በማለት አመለከተ፡፡

    ‹‹ስለራስህ መብት ብቻ ተናገር ስለፍርድ ቤቱ ተወው›› በማለት፣ ያላቸውን ማመልከቻ በጠበቆቻቸው አማካይነት ጽፈው እንዲያቀርቡ በማዘዝ፣ የዓቃቤ ሕግን የሰዎች ምስክርነት ለመስማት ለታኅሣሥ 16 ቀን 2004 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡

    Views: 616 | Added by: dani | Rating: 4.0/1
    Total comments: 0
    Name *:
    Email *:
    Code *:
    Copyright MyCorp © 2024
    Create a free website with uCoz