የኖርዌይ መንግሥት እና ዓለም አቀፉ የኃይል አቅርቦት ጉዳይ ተመልካች ድርጅት በጋራ ያዘጋጁት ይኸው የሁለት ቀናት ጉባዔ የኃይል አቅርቦትን በተለይ በአዳጊዎቹ ሀገሮች ላሉት ለድሆች ማዳረስ የሚቻልበት ዘዴ እንዴት ሊሻሻል ይችላል ለሚለው ሀሳብ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየተወያየ ነው።የጉባዔው አዘጋጂዎች ብራዚል፡ ኢትዮጵያ፡ ሕንድ፡ ላይቤሪያ እና ደቡብ አፍሪቃ ይህንኑ ሀሳብ ተግባራዊ ለማድረግ በጀመሩት ጥረታቸው ላይ አብረው በአጋርነት እንዲሰሩም ጋብዘዋቸዋል። ጉባዔው በሚካሄድባት በኖርዌይ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን በኦስሎ ከተማ ጉባዔው በሚደረግበት አዳራሽ ደጃፍ በመሰብሰብ በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ አንጻር ተቃውሞ ሰልፍ አካሂደዋል። የተቃውሞ ሰልፉን ያዘጋጀውን የኢትዮጵያውያኑን የግብረ ኃይል የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዶክተር ሠይፉ ፀጋዬን አርያም ተክሌ በስልክ አነጋግራዋለች፤ በመጀመሪያም የተቃውሞ ሰልፉ ዓላማን እንዲያብራሩላት ጠይቃቸዋለች።
አርያም ተክሌ
ሸዋዬ ለገሠ