Thursday, 2024-05-02, 3:06 AM
ETHIOPIAN POLITICS current event and news
Main Registration Login
Welcome, Guest · RSS
Site menu
    news
    news
    curency
    Calendar
    «  January 2012  »
    SuMoTuWeThFrSa
    1234567
    891011121314
    15161718192021
    22232425262728
    293031
    Site friends
     
    Main » 2012 » January » 10 » የኦፌዴን እና የኦህኮ አመራሮች ከወራት እስር በኋላ በአሸባሪነት ተከሰው ፍርድ ቤት ቀረቡ by Addis Neger on Tuesday, 10 January 2012 at 01:46
    4:55 PM
    የኦፌዴን እና የኦህኮ አመራሮች ከወራት እስር በኋላ በአሸባሪነት ተከሰው ፍርድ ቤት ቀረቡ by Addis Neger on Tuesday, 10 January 2012 at 01:46

     

    (ሙሉ ገ./ አዲስነገርኦንላይን)

     

    ሰኞ ታህሳስ 30 ቀን 2004 ዓ.ም፡- የኢሕአዴግ መንግሥት በእነ በቀለ ገርባ የክስ መዝገብ በአሸባሪነት ወንጀል በከሰሳቸው በኦፌዴን እና በኦህኮ ፓርቲ የአመራር አባላት ላይ ዐቃቤ- ሕግ 9 የሰው ምስክሮችን ዛሬ ለሙሉ ቀን አቀረበ፡፡ 14 ሰዎችን ደግሞ ነገ ጠዋት ጥር 1 ቀን 2004 ዓ.ም ምስክር አድርጎ ያቀርባል፡፡

     

    በከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ጠባቡ አዳራሽ ውስጥ በተካሄደው ችሎት ላይ የኦፍዴን ፓርቲና የመድረክ የአመራር አባል አቶ በቀለ ገርባ፣ የኦህኮ ፓርቲና የመድረክ የአመራር አባል አቶ ኦልባና ለሊሳ፣ አቶ ወልቤካ ለሚ፣ አቶ አደም ቡሳ፣ ወ/ሪት ሀዋ ዋቆ፣ አቶ መሐመድ መሉ፣ አቶ ደረጀ ከተማ፣ አቶ አዲሱ ምክሬ እና አቶ ገልገሉ ጉፉ የእምነት ክህደት ቃል በፍርድ ቤት ሲጠየቁ በሰላማዊ መንገድ በተቃውሞ የፖለቲካ ፓርቲ እንቅስቃሴ ውስጥ በመሳተፋቸው ብቻ መንግሥት የሐሰት ክስ እንደመሠረተባቸው ገልጸዋል፡፡

     

    ፍርድ ቤቱ የግል ጠበቃ ማቆም ላልቻሉ ተከሳሾች ከተከላካይ ጠበቆች ጽ/ቤት መንግሥት እንዲያቆምላቸው መሐላ አስፈጽሞ ሲያበቃ በእለቱ ከጠበቃ ጋር ላልተመካከሩ ተከሳሾች የ30 ደቂቃ የምክክር ጊዜ ፈቅዶ የዐቃቤ ሕግ ዘጠኝ ምስክሮች ለሙሉ ቀን እንዲቀርቡ አድርጓል፡፡ የሰነድ ማስረጃዎቹም ለነገ እንዲቀርቡለት አዟል፡፡

     

    የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ የኢሕአዴግ አባል የሆኑ መምህራንን፣ በአነስተኛና ጥቃቅን የተደራጁ የኢሕአዴግ አባላትን፣ የክፍለ ከተማና የዞን የአስተዳደር ሠራተኞችን እና ታማኝ የመንግሥት ሠራተኞች አባላቱን በምስክርነት አቅርቧል፡፡

     

     

    የዐቃቤ ሕግ የመጀመሪያ ምስክር ተደርጎ የቀረበው አቶ ጌትነት ተካ የቴአትርና የፊልም ባለሙያ ነኝ ያለ ሲሆን በኦህኮ ፓርቲ አመራር በአቶ ኦልባና ላይ ታዛቢ ምስክር መሆኑን ገልጾ የመኖሪያ ቤቱ ሲፈተሸ የተለያዩ በኦሮምኛ ቋንቋ የተጻፉ የኦነግ ሰነዶች፣ ሲዲዎች፣ የኦነግ አርማ ያለበት የኦሮሞ የባህል ልብስ ለብሶ የተነሳውን ፎቶ መመልከቱንና በፖሊስ በኤግዚቢትነት መያዙን መስክሯል። የተከሳሽ ጠበቃ ባነሱት መስቀለኛ ጥያቄ ላይ የኦነግን አርማ ከዚህ ቀደም እንደማያውቅና ለይ ቢባል መለየት እንደማይችል፣ ኦሮምኛ ቋንቋ እንደማይችልና ተገኙ የተባሉትን ሰነዶች አለማንበቡንና ይዘታቸውን አለማወቁን ነገር ግን ፖሊሶች የኦነግ አርማ መሆኑንና የኦነግ ሰነድ መሆኑን እንደነገሩት ገልጿል፡፡ አንድ የኦነግ አርማ ያለበትን ሰነድ ፖሊሶቹ ከቤቱ አነሳን በማለት አቶ ኦልባ እንዲፈርምበት ሲጠየቁት "ይህን እኔ አላቀውም፤ እናንተ ናችሁ ያመጣችሁብኝ” ሲል ፖሊሶችን ተናግሮ አልፈርምም ብሏል በማለት መስክሯል፡፡

     

    የዐቃቤ- ሕግ ሦስተኛ ምስክር ሆኖ የቀረበው በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የገላን ትምህርት ቤት መምህር መሆኑን የጠቀሰው አቶ ኢዮሲያስ አበራ የኦፌዴን ፓርቲ ከፍተኛ የአመራር አባል የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በክረምት የመምህራን ትምህርት ስልጠና ላይ የመመረቂያ ጽሑፉን ሲሰራ አማካሪው እንደነበሩ ተናግሯል። "አንድ ቀን ከሁለት ጓደኞቼ ጋር ቢሯቸው የጥናት ወረቀታችንን ልንሰጣቸው ስንገባ የኢሕአዴግ መንግሥት ሦስት ብሔሮችን ኦሮሞን፣ ሶማሌንና የደቡብ ሕዝቦችን አጥብቆ ስለሚጠላ በ2004 ዓ.ም በየትምህርት ቤታችን ማስተማር ስንጀምር ሁከትና አመጽ ተማሪዎች ላይ በማነሳሳት መንግሥትን እንድናወርድ አነሳስተውናል” ብሎ መስክሯል። አቶ በቀለ ገርባ "በዚህ ፍርድ ቤት መብት ካለኝ ምስክሩን ራሴ እንድጠይቀው ፍርድ ቤቱ ይፍቀድልኝ” ብለው ቢጠይቁም ፍርድ ቤቱ "ጠበቃው ውክልናቸውን ካነሱና በግሌ እከራከራለሁ ካሉ ብቻ ነው የሚፈቀድልዎት” ብሎ ከልክሏቸዋል፡፡

     

    የተከሳሽ ጠበቃ ከአቶ በቀለ ጋር ከተመካከሩ በኋላ ለምስክሩ መስቀለኛ ጥያቄዎችን ያቀረቡ ሲሆን  "ለመሆኑ ከአቶ በቀለ ጋር የውይይት ክበብ ነበራችሁ እንዴ፣ እንዴት በአንድ ጊዜ እንዲህ ያለ ሲሪየስ ጉዳይ አወሩህ?” ብለው ሲጠይቁት "ለእኔም የደነቀኝ እርሱ ነው፤ እኔ ብሆን ለማላውቀው ሰው እንዲህ አላወራም” በማለት መልሷል፡፡

     

    የተከላካይ ጠበቃ ምስክሩን "እባክዎን እውነቱን ይናገሩ፣ እውነት ለመናገር ነው መሐላ የፈጸሙት” በማለት የተናገሩ ሲሆን ዐቃቤ ሕግ "ምስክሬን አስፈራሩብኝ” በማለቱ ፍርድ ቤቱ መስቀለኛ ጥያቄዎችን ብቻ እንዲያቀርቡ አዟል። የተከሳሽ ጠበቃው "አንተ ወደ አቶ በቀለ ቢሮ የመጣህ ጊዜ እኔ የኢሕአዴግ አባል ነኝ ነገር ግን የእናንተ ፓርቲ አባል መሆን እፈልጋለሁ ብለህ ጠይቀሃቸው ነበር” በማለት ሲጠይቁት "አላልኩም፤ እንዲህ ብዬ አልመሰከርኩም” በማለቱ ዐቃቤ ሕግ አሁንም ደንበኛዬ ከመሰከረው ውጪ መስቀለኛ ጥያቄ እየተጠየቀብኝ ነው ብሎ ያቀረበውን አቤቱታ ፍርድ ቤቱ ተቀብሎታል፡፡        

    ችሎቱ ነገ ማክሰኞ ቀሪዎቹን ምስክሮች ለማዳመጥ ቀጠሮ ይዟል።

    Views: 632 | Added by: dani | Rating: 5.0/1
    Total comments: 0
    Name *:
    Email *:
    Code *:
    Copyright MyCorp © 2024
    Create a free website with uCoz