Wednesday, 2024-04-24, 7:40 PM
ETHIOPIAN POLITICS current event and news
Main Registration Login
Welcome, Guest · RSS
Site menu
    news
    news
    curency
    Calendar
    «  October 2011  »
    SuMoTuWeThFrSa
          1
    2345678
    9101112131415
    16171819202122
    23242526272829
    3031
    Site friends
     
    Main » 2011 » October » 1 » ፍኖት - የአገዛዙ ኢፍትሃዊ በትር ያረፈባቸዉ አቶ በቀለ ገርባ ማን ናቸዉ ? September 30th, 2011
    3:04 PM
    ፍኖት - የአገዛዙ ኢፍትሃዊ በትር ያረፈባቸዉ አቶ በቀለ ገርባ ማን ናቸዉ ? September 30th, 2011

    አቶ በቀለ ገርባ በ1954 ዓ.ም በወለጋ ክፍለ ሀገር ልዩ ቦታው ቦጂ ድርመጂ በሚባል አካባቢ ተወልደው የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በዚያው አካባቢ አጠናቀዋል፡፡ ከዚያም በጤና ረዳትነት በመማር አሁን ደቡብ ክልል ጌዲኦ ዞን በሚባል ቦታ ለረጅም ዓመታት አገልግለዋል፡፡

    ይህ በእንዲህ እንዳለ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እንግሊዘኛ ቋንቋ በመማር የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ድግሪያቸውን (BA&MA)አግኝተው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ውስጥ በመምህርነት እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በእንግሊዘኛ የፍልስፍና ዲግሪ (PhD) እያጠኑ እንደነበር ለማወቅ ችለናል፡፡ በሥራ ዓለምም ለ20 ዓመታት አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን ጨምሮ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች ውስጥ አገልግለዋል፡፡

    የቤተሰብና ማህበራዊ ህይወት
    አቶ በቀለ ገርባ ባለትዳርና የአራት ልጆች አባት ሲሆኑ አንድ ሴትና ሦስት ወንድ ልጆች አሏቸው፡፡ የመጀመሪያ ልጃቸው ሴት ስትሆን የመጀመሪያ ዲግሪዋን ከአንድ የመንግስት ዩኒቨርስቲ ጨርሳ በ2003 ዓ.ም ተመርቃለች፡፡ የሁለተኛ ልጃቸው ወንድ ሲሆን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ጨርሶ ጥሩ ውጤት አምጥቶ ዩኒቨርስቲ ምደባን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡ ሦስተኛ እና አራተኛ ልጆቻቸው መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ላይ ይገኛሉ፡፡
    ባለቤታቸው ወ/ሮ ሐና ረጋሳ ይባላሉ፡፡ አቶ በቀለ ምንም እንኳ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቢሰሩም የመኖሪያ አድራሻቸውና ቤተሰቦቻቸው የሚገኙት ናዝሬት ከተማ ነው፡፡ ቤተሰቦቻቸውንም ከአዲስ አበባ እየተመላለሱ እንደሚጠይቋቸው ባለቤታቸው ተናግረዋል፡፡ በማህበራዊ ህይወታቸውም ከሰው ጋር ተግባቢና ሐሳባቸውን በነፃነት የሚገልፁ፣ በተለይ በተማሪዎቻቸው እጅግ የሚወደዱና እንደ ልጆቻቸው እንደሚያቀርቡ፤ የሰውን ሐሳብ በቀላሉ የሚረዱና ቀና አመለካከት ያላቸው ናቸው ይላሉ ባልደረቦቻቸው፡፡ ከማንኛውም ደባል ሱስ ነፃ መሆናቸው ደግሞ ይበልጥ እንዲወደዱ አድርጓቸዋል ይላሉ፡፡

    የፖለቲካ ህይወታቸው
    ፓለቲካን መቼ እንደጀመሩ በግልፅ ባይታወቅም ከወጣትነታቸው ጀምሮ እንደሆነ የሚታወቅ ሲሆን ይበልጥ ግን የኦሮሞ ፌደራሊስት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄን (ኦፌዲን)ን ከተቀላቀሉ በኋላ ጐልተው እንደወጡ ይነገራል፡፡ በድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ በመሆንና በመድረክ ፓርቲ ውስጥም የሥራ አስፈፃሚ አባል በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ ነገር ግን ከኦነግ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብሎ መጠርጠራቸው ከእውነት የራቀ ነው፡፡ ምክንያቱም እንደማንኛውም ጨዋ ኢትዮጵያዊ በኃይማኖት ታንፀው ያደጉ በመሆናቸው እንኳን የኦነግ አባል ሊሆኑ ቀርቶ ኦፌዲንን እራሱ ቀስ ብለው ነው የተቀላቀሉት ፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት ለሰላማዊ ትግል ትልቅ ቦታ ስለሚሰጡ ነው ሲሉ ዶ/ር ሞጋ ተናግረዋል፡፡ ሌላው "ሽብር ለተባለው እሱ እኮ በባህልና በኃይማኖት ታንፆ ያደገ እና ከተለያዩ የሀገራችን ማህበረሰቦች ጋር በተለያየ ቦታ በጥሩ መግባባትና ፍቅር አብሮ እየኖረ ነው፡፡ ስለዚህ ማን ላይ ሽብር ያስባል? እንኳን ማሰብ በሌሎች ሀገሮች ላይ የሚፈፀመውን የሽብር ተግባር በመገናኛ ብዙኃን ሲያይና ሲሰማ የሚሳቀቅና የሚናደድ ሰው ነው፡፡ እኛ አሁን በጋብቻ ዓለም ውስጥ ሰንኖር 21ኛ ዓመታችን ነው ከተጠረጠረበት ተግባር ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንደሌለው ጠንቅቄ አውቀዋለሁ” ሲሉ ባለቤታቸው ወ/ሮ ሐና ይናገራሉ፡፡ የመድረክ በተለይም የኦፌዴን አጋሮቻቸውም የወ/ሮ ሐና ረጋሳን ሐሳብ ይጋራሉ፡፡

    ሕወሃት ኢሕአዴግ ኢቲቪን፣ ራዲዮዉን በሙሉ ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ አፍኖ ይዟል። የአንድነት ፓርቲ በፍኖት ጋዜጣ ሕዝቡን ለመድረስ፣ ለማስተማር እየሞከረ ነዉ። ጋዜጣዉን በብዛት ለማሳተም፣ በአገሪቷ ክፍሎች በስፋት ለማሰራጨት የገንዘብ አቅም ይጠይቃል። ለዚህ ኢትዮጵያዊ አላማ የድርሻዎትን ይወጡ ዘንድ አገራዊ ጥሪ እናቀርባለን። በገንዘብዎት አገር ቤት የሚደረገዉን ትግል ይርዱ።

    Views: 773 | Added by: dani | Rating: 4.0/1
    Total comments: 0
    Name *:
    Email *:
    Code *:
    Copyright MyCorp © 2024
    Create a free website with uCoz