Tuesday, 2018-12-11, 11:14 PM
ETHIOPIAN POLITICS current event and news
Main Registration Login
Welcome, Guest · RSS
Site menu
  news
  news
  curency
  Calendar
  «  September 2011  »
  SuMoTuWeThFrSa
      123
  45678910
  11121314151617
  18192021222324
  252627282930
  Site friends
   
  Main » 2011 » September » 28 » ፍኖት - የአገዛዙ ኢፍትሃዊ በትር ያረፈባቸዉ አቶ ኦልባና ሌሊሳ ማን ናቸዉ ? September 27th, 2011
  1:30 PM
  ፍኖት - የአገዛዙ ኢፍትሃዊ በትር ያረፈባቸዉ አቶ ኦልባና ሌሊሳ ማን ናቸዉ ? September 27th, 2011

  አቶ ኦልባና ሌሊሳ በምዕራብ ሸዋ ጨሊ ወረዳ በ1966 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውንም በተወለዱበት አካባቢ አጠናቀው ወደ መንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በመግባት በግብርና ዲፕሎማ አግኝተዋል፡፡ ከዚያም በመንግሥት ግብርና ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ውስጥ በሚተዳደር መስሪያ ቤት ተቀጥረው ለዓመታት አገልግለዋል፡፡ በማታው መርሐ ግብር በአምቦ ዩኒቨርስቲ የትምህርት ደረጃቸውን ለማሻሻል እየተማሩ እንደነበርና በተደረገባቸው የፖለቲካ ጫና ምክንያት ሥራቸውን በፈቃዳቸው ሲለቁ የጀመሩትንም ትምህርት ለማቋረጥ እንደተገደዱ ባልደረቦቻቸው ይናገራሉ፡፡

  የቤተሰብ ሁኔታን በተመለከተ እስካአሁን ትዳር ያልያዙ ሲሆን መተዳደሪያቸውም ሙሉ በሙሉ የፖለቲካ ሥራ ስለሆነ ከኦህኮ ጽ/ቤት በሚያገኙት አባል ነው፡፡

  የፖለቲካ ህይወት ከ1992 ዓ.ም ምርጫ በፊት የተወለዱበት ጨሊያ ወረዳን በመወከል ለፓርላማ ተወዳድረዋል፡፡ 1997 ዓ.ም ደግሞ ለኦሮሚያ ም/ቤት ድርጅታቸውን ወክለው በመወዳደር ተመርጠው ለ5 ዓመታት አገልግለዋል፡፡ በተጨማሪም በወቅቱ የህብረት ዋና ተጠሪ ነበሩ፡፡ በምርጫ 2002 ደግሞ ለኦሮሚያ ም/ቤት ተወዳድረዋል፡፡ ከ1996 ዓ.ም ጀምሮ የኦህኮ ምክትል የቢሮ ኃላፊ ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ "በሥነ -ምግባርና በኃይማኖት ታንፀው ስላደጉ ከማህበረሰቡ ጋር ጥሩ መግባባት ያላቸው ሲሆን ትዕግስተኛ እና ከሰዎች ጋር በሰላም መወያየትና ችግርን በመግባባት መፍታት ስለሚያምኑ በሰላም መነጋገር አንዱ መለያ ባህሪያቸው ነው” ሲሉ ዶ/ር መረራ ጉዲና ተናግረዋል፡፡

  "የተጠራጠሩበት ጉዳይ ዛሬ የመጀመሪያ ሳይሆን በተደጋጋሚ አምቦ ላይ ይፈፀምባቸው እንደነበርና ነፃ ሆነው እንደተለቀቁ ይታወቃል” በማለት ከምርጫ 97 በኋላም ተደጋጋሚ ዛቻና ማስፈራራት ይደርስባቸው እንደነበርና ከዚህ በፊት እንጦጦ ጫካ ተወስደው ከባድ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው የትግል አጋሮቻቸው አስታውሰዋል፡፡

  "አሁን በሽብር መጠርጠራቸው ሆን ተብሎ ትግሉን ለማዳከም እንደሆነ እንጂ አቶ ኦልባና ሰላማዊ ትግልን እንደ መርሃቸው የሚቆጥሩና የቆዩ ፖለቲከኛ ናቸው እንጂ የሽብር ዓላማማም ሆነ ትብብር እንደሌላቸው ይታወቃል” ሲሉ ዶ/ር መረራ ለዝግጅት ክፍሉ ተናግረዋል፡፡ በዚህ ወቅት የኦህኮ /መድረክ አመራር ውስጥም ጉልህ ተሳትፎ የሚያደርጉና ከሥራ ባልደረቦቻቸውም ሆነ ከሌሎች ጓደኞቻቸው ጋር ጥሩ የሆነ ማህበራዊ ግንኙነት ያላቸው ናቸው ሲሉ የትግል አጋሮቻቸው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

  ሕወሃት ኢሕአዴግ ኢቲቪን፣ ራዲዮዉን በሙሉ ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ አፍኖ ይዟል። የአንድነት ፓርቲ በፍኖት ጋዜጣ ሕዝቡን ለመድረስ፣ ለማስተማር እየሞከረ ነዉ። ጋዜጣዉን በብዛት ለማሳተም፣ በአገሪቷ ክፍሎች በስፋት ለማሰራጨት የገንዘብ አቅም ይጠይቃል። ለዚህ ኢትዮጵያዊ አላማ የድርሻዎትን ይወጡ ዘንድ አገራዊ ጥሪ እናቀርባለን። በገንዘብዎት አገር ቤት የሚደረገዉን ትግል ይርዱ።

  Views: 584 | Added by: dani | Rating: 4.0/1
  Total comments: 0
  Name *:
  Email *:
  Code *:
  Copyright MyCorp © 2018
  Create a free website with uCoz