Tuesday, 2018-12-11, 11:13 PM
ETHIOPIAN POLITICS current event and news
Main Registration Login
Welcome, Guest · RSS
Site menu
  news
  news
  curency
  Calendar
  «  September 2011  »
  SuMoTuWeThFrSa
      123
  45678910
  11121314151617
  18192021222324
  252627282930
  Site friends
   
  Main » 2011 » September » 28 » ፍኖት - የተፈጸመበትን ኢ-ሰብአዊ ድርጊት በማየቴ እጅግ አዝኛለሁ፡፡ ለአገርና ለሕዝብ የሚከፈል መስዋዕትነት በመሆኑ ኩራት ይሰማኛል (ወ/ት ሊዲያ የአቶ ዘሪሁን ልጅ) September 27th, 2011
  1:28 PM
  ፍኖት - የተፈጸመበትን ኢ-ሰብአዊ ድርጊት በማየቴ እጅግ አዝኛለሁ፡፡ ለአገርና ለሕዝብ የሚከፈል መስዋዕትነት በመሆኑ ኩራት ይሰማኛል (ወ/ት ሊዲያ የአቶ ዘሪሁን ልጅ) September 27th, 2011

  ወ/ት ሊዲያ ዘሪሁን ትባላለች፡፡ በእስር ላይ የሚገኙት የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ /ኢብአፓ/ ፕሬዝደንት የአቶ ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔር ልጅ ናት፡፡ በአባቷ ዙሪያ ባልደረባችን ብዙአየሁ ወንድሙ አነጋርሯታል፡፡ መልካም ቆይታ፡፡

  አባትሽ አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔር በእስር ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡ በመጀመሪያ አቶ ዘሪሁን የት ተወለዱ?
  ወ/ት ሊዲያ- ዘርዬ የተወለደው እዚሁ አዲስ አበባ ከተማ ልዩ ሥፍራው መርከቶ የሚባል አካባቢ ነው፡፡

  ስለ ትምህርታቸው አጠቃላይ ሁኔታ ብትገልጪልኝ 
  ከ1-12ኛ ክፍል ተመሮ ትምህርቱን ያጠናቀቀው ጉለሌ በሚገኘው መድኃኔዓለም የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤትና በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ነው፡፡ ከኢትዮጵስ ኮሌጅ በዲፕሎማ ተመርቋል፡፡ ከእንግሊዝ አገር በተልዕኮ ትምርት ተመሮ መመረቁን አውቃለሁ፡፡

  አቶ ዘሪሁን ስንት ልጆች አሏቸው? አንቺ ስንተኛ ልጃቸው ነሽ? ከቤተሰባቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዴት ትገልጪዋለሽ?ሁለት ልጆች ነው ያለነዉ፡፡ እኔ ሁለተኛ ልጅ ነኝ፡፡ በአኔና በታላቄ መካከል ያለው ልዩነት አንድ ዓመት ነው፡፡ ታላቅና ታናሽ ሳይሆን አኩዮች ነን፡፡ አንደንድ ሰዎች መንታዎች ናችሁ እያሉ ይጠይቁናል፡፡ እናትና አባታችንም በልጅነታቸው ስለወለዱን አብረን ስንታይ ወላጆቻችን ሳይሆኑ ጓደኞቻችን ይመስላሉ፡፡ የማያውቁን አብረውን ሲያዩን ጓደኞቻችን አድርገው ይወስዱታል፡፡ በመልክና በዕድሜ ብቻ ሳይሆን በመቀራረብም አንደ ጋደኛ ነን፡፡ ዘርዬ ያሳደገን አቅርቦ በፍቅር ነው፡፡ እኛም ለአባታችንና ለእናታችን ልዩ ፍቅር አለን፡፡ አስከ ዛሬም ከአጠገባችን ተለይቶን አያውቅም፡፡

  አቶ ዘሪሁን መደበኛ ሥራቸው መንድነው? 
  አነስተኛ ንግድ ሥራ ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ በፖለቲካው ሥራ ያሳልፋል፡፡

  ሥራውን አሁን እናንተ ቀጥላችሁበታል?ሥራው ቆሟል፡፡ ከአባታችን አናገኝ የነበረው ገቢ ተቋርጧል፡፡

  ከልጆቹ ሥራ የያዘ ሰው አለ?የለም፡፡

  ለምን የእሳቸውን ሥራ እናንተ አልቀጠላችሁም? 
  ሥራውንም አናውቀውም፡፡ በመስመሩ ውስጥ አልገባንም፡፡ እሱ ሲሰራ የነበረው ከዱባይና ከቻይና ዕቃ የሚያመጡ ነጋዴዎችን እየተቀበለ ለቸርቻሪ ነጋዴዎች ማከፋፈል ነው፡፡ እኛ እንዳንቀጠልበት በመስመሩ ውስጥ አልገባንም፡፡ ይህንን ሥራ ለመስራት መተዋወቅ መግባባትና መተማመንን ይጠይቃል፡፡

  አሁን በምን ትተዳደራላችሁ? 
  እናታችን በአንድ የግል ድርጅት ውስጥ በአነስተኛ ደሞዝ ትሠራለች፡፡ በአሁኑ ጊዜ በእሷ ገቢ ነው የምንኖረው፡፡

  አቶ ዘሪሁን ከጓደኞቻቸውና ከአካባቢ ሕብረተሰብ ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዴት ትገልጪዋለሽ?
  ያደገው መርካቶ በመሆኑ ከሰው ጋር ለመግባባት ጊዜ አይወስድበትም፡፡ ፈጣን፣ተጫዋች፣ሩህሩህና ከሰው ጋር መሥራት የሚችል፣ከሰው ጋር ተካፍሎ መብላት የሚወድ ሰው ነው፡፡ ኪሱ ውስጥ ያለው ገንዘብ አስኪያልቅ ድረስ ሰው የሚጠግብ አይመስለውም፡፡ አብረን መንገድ ላይ ስንሄድ ብዙ ጊዜ ስለሚያቆመን እንቸገራለን፡፡ መንገድ ላይ ያገኘው ሁሉ ዘርዬ፣ ዘሬ እያለው ትልቁም ትንሹም ሲንጠላጠልበት ማየት የተለመደ ነው፡፡ ዘርዬ ፍቅር የሆነ አባት ነው፡፡

  አባትሽ ወደ ፖለቲካው ሕይወት መቼና እንዴት እንደገቡ የምታውቂው ነገር ይኖራል? 
  አዎ ዘርዬ ለእኛ የሚደብቀው ታሪክ የለውም፡፡ እንደነገረን ወደ ፖለቲካው ሕይወት ያዘነበለው በቀድሞ መንግሥት ነው፡፡ ገና በ15 በ16 ዓመቱ በቀድሞ መንግሥት በአብዮታዊ ኢትዮጵያ ወጣቶች ማህበር/አኢወማ/ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ያደርግ እንደነበር፤ ኢህአዴግ አገሪቱን ተቆጣጥሮ ፓርቲዎች ሲቋቋሙ በመላው አማራ ሕዝብ /መአህድ/ ውስጥ ተደራጅቶ ታግሏል፡፡ ከፕ/ር አስራት ሞት በኋላ በመአህድ ውስጥ አለመግባባት በመፈጠሩ መአህድን ለቆ በመውጣት ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሕብረት/ኢዲህ/ ገብቶ ነበር፡፡ ኢዲህ ከኢዴፓ ጋር ሲቀላቀል ቅልቅሉን በመቃወም ራሱን ከድርጅቱ አገላለ፡፡

  በመጨረሻ ከተወሰኑ የትግል አጋሮቹ ጋር በመሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲን /ኢብአፓ/ን መሠረቱ፡፡ ፓርቲው ከተመሠረተበት ጀምሮ በፕሬዝደንትነት በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡

  በመታሰራቸው ምን ይሰማሻል?
  ዘርዬ ተነጥሎን ስለማያውቅና ከታሰረም በኋላ የተፈጸመበትን ኢ-ሰብአዊ ድርጊት በማየቴ እጅግ አዝኛለሁ፡፡ ለአገርና ለሕዝብ የሚከፈል መስዋዕትነት በመሆኑ ኩራት ይሰማኛል፡፡

  አባትሽ ታሰሩ የተባሉት "በሽብርተኝነት” ነው፡፡ "በልማት አውታሮች ላይ አደጋ ለማድረስ ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸው ነው” ተብሏል፡፡ ታዲያ ይህ እንዴት ሊያኮራ ይችላል ?
  እኔ ይህንን አላምንበትም፡፡ በሽብር - ተግባር ውስጥ ይገባል ይሳተፋል ብዬም አላስብም፡፡ አባቴን በደንብ አውቀዋለሁ፡፡ በሐዝብ ሀብትና ንብረት ላይ ውድመት ለመፈጸም በሰው ሕይወት አደጋ እንዲፈጠር ሊተባበር አይችልም፡፡ ሽብርተኞች እኮ ከሰብአዊ አመለካከት ውጪ የሆኑ ናቸው፡፡ ስለ ሰው ልጅ ደንታ የሌላቸው ሱሰኞቹ ናቸው፡፡ ዘርዬ ግን አይደለም፡፡ ለሰው ፍጡር ትልቅ ክብር ያለው ነው፡፡ ወንጀልን በመከላከል ሥራ የሚሳተፍ እንጂ ወንጀል ለመፈጸም ተፈጥሮውም ባህርዩም አይፈቅድም፡፡

  አንቺ በምን ምክንያት ታሰረ ብለሽ ታምኛለሽ? 
  የአባቴ ፓርቲ የምርጫውን ሥን ምግባር አልፈርምም ብሎ አቋም ከወሰዱት ፓርቲዎች የመጀመሪያው ተቃዋሚ ፓርቲ ነው፡፡ የምርጫውን ውጤትም አልቀበልም ብሎ አቋሙን በግልጽ የወሰደ ፓርቲ ነው፡፡ ከምርጫው በኋላ በርካታ የፓርቲው አባላት ከሥራ ታግደዋል፡፡ እርዳታ ተከልክለዋል፡፡ ወከባ ዛቻ ይፈፀምባቸው እንደነበረ በተደጋጋሚ ሲናገር ሰምቻለሁ፡፡ የፓርቲውን መግለጫዎች አንብቤአለሁ፡፡ ግንቦት 2ዐን ቀን በመቃወም ሕዝባዊ ሠለማዊ ሠልፍ ለማድረግ ፈቃድ ጠይቀው ነበር፡፡ የአሜሪካን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ሂላር ክሊንተን አዲስ አበባ ሲመጡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የፖለቲካ ሁኔታና የሚፈጸመውን ኢ-ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ ጥሰት ለመግለጽ እንዲችሉ ፕሮግራም አንደያዝላቸው ኢንባሲውን በጽሑፍ ጠይቀዋል፡፡ በዚህ ምክንያት የተፈፀመበት ጥቃት ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ በእርግጠኝነት ዘርዬ የታሰረው ኢህአዴግን አምርሮ በመታገሉ ነው፡፡ የታሠረው በአመለካከቱ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡

  ይህንን ሁሉ አንቺ እንዴት ልታውቂ ቻልሽ? 
  እኔ የዕለት ተዕለት ሁኔታ እከታተላለሁ፡- ፡ የፓርቲውንና የአባቴን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ጠንቅቄ አውቃለሁ፡፡

  አቶ ዘሪሁን አሁን ያሉበት ሁኔታ እንዴት ነው? 
  አሁን ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ነው፡፡ - እንደ አንድ እስረኛ ተይዟል፡፡ ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ በነበረበት ጊዜ ኢሰብአዊ የሆነ ድርጊት ተፈጽሞበታል፡፡ ሁለት ቀን ሙሉ እጁ ታስሮና ተሰቅሎ የማያውቀውንና ያልፈፀመውን እንዲያምን ሲደበደብ እንደነበር ለፍ/ቤት ሲያስረዳ ሰምቻለሁ፡፡ የተፈጸመበትን ግፍ ለቤተሰቡም ገልጿል፡፡ ለህግ ቆሜአለሁ፣ህግ አስከባሪ ነኝ ከሚል አካል ህግ እናውቃለን ህገ-መንግሥትን እናከብራለን ከሚሉ ወገኖች እንዲህ ዓይነት ግፍ በማየቴ አዝናለሁ፡፡ ስለ ህግ የበላይነት ስለ ፍትህ ስለ ሰብአዊ መብትና ዴሞክራሲ ለማውሪት ምን ሞራል አላቸው? ጠባሳውን አሁንም ማየት ይቻላል፡፡

  ፍ/ቤቱ ይህንን ሲሰማ ምን አለ? ድብደባው ይቁም፡፡ ህክምና ይደረግለት ብሏል፡፡ በዚህም አዝኜአለሁ፡፡ አንድን በሕግ ቁጥጥር ሥር ያለን ሰው እንዲህ አይነት ግፍ የፈጸመ ለምን በህግ አይጠየቁም? ለምን እርምጃ አይወስዱም? ይህ ድርጊት ከተፈጸመ ሁለት ወር አልፎታል፡፡ ህክምና አላገኘም፡፡ ህመሙ ዛሬም ይሰማዋል፡፡ድብደባው ይቁም ብሎ ብይን በቂ አይደለም፡፡

  ፖለቲካ ውስጥ ባይገባ ይህ ሁሉ አይገጥመውም ነበር አሁን ላይ ሆነሽ ስታስቢው በፖለቲካ ውስጥ ባይገባ ኖሮ ብለሽ አታስቢም? በፍፁም አላስብም፡፡ ፖለቲካ ውስጥ የገባው አገሪቱ ውስጥ ያለው ፖለቲካ ሁኔታ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ እየከፈለ ያለው መስዋዕትነት አንድ ክቡር ዜጋ ለአገሩ የሚከፍለው ነው፡፡ ለአገርና ለህዝብ የሚከፈል ዋጋ ከምንም በላይ ክብር አለው ብዬ አስባለሁ፡፡ የእሱ መታሰር መደብደብ መሰቃየት የእኛም መጉላላትና ለችግር መጋለጥ ከሕዝብና ከአገር ጥቅም ጋር ሲወዳደር ሚዛን የሚጻፉ አይደሉም፡፡

  አባትሽ በመታሰሩ በኑሮአችሁ ላይ የፈጠረው ችግር አለ?
  የቤተሰብ የገቢ ምንጭ ሲቋረጥ የሚፈጠረውን ለማንም ግልጽ ነው፡፡ የኑሮ ውድነቱ ከዕለት ተዕለት የምትመለከተው ነው፡፡ ችግራችንን ተቋቁመን አቅማችን በፈቀደው ሁሉ ዘርዬን ባለበት ለመርዳት እየሞከርን ነዉ።

  ሕወሃት ኢሕአዴግ ኢቲቪን፣ ራዲዮዉን በሙሉ ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ አፍኖ ይዟል። የአንድነት ፓርቲ በፍኖት ጋዜጣ ሕዝቡን ለመድረስ፣ ለማስተማር እየሞከረ ነዉ። ጋዜጣዉን በብዛት ለማሳተም፣ በአገሪቷ ክፍሎች በስፋት ለማሰራጨት የገንዘብ አቅም ይጠይቃል።፡ለዚህ ኢትዮጵያዊ አላማ የድርሻዎትን ይወጡ ዘንድ አገራዊ ጥሪ እናቀርባለን። በገንዘብዎት አገር ቤት የሚደረገዉን ትግል ይርዱ

  Views: 654 | Added by: dani | Rating: 4.0/1
  Total comments: 0
  Name *:
  Email *:
  Code *:
  Copyright MyCorp © 2018
  Create a free website with uCoz