Friday, 2024-04-19, 4:05 PM
ETHIOPIAN POLITICS current event and news
Main Registration Login
Welcome, Guest · RSS
Site menu
    news
    news
    curency
    Calendar
    «  September 2011  »
    SuMoTuWeThFrSa
        123
    45678910
    11121314151617
    18192021222324
    252627282930
    Site friends
     
    Main » 2011 » September » 26 » አዉራምባ - ርእስ አንቀጽ ፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ እየተፈፀመብን ያለውን ደባ ይረዳልን September 26th, 2011
    11:27 PM
    አዉራምባ - ርእስ አንቀጽ ፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ እየተፈፀመብን ያለውን ደባ ይረዳልን September 26th, 2011

    ‹‹ … የዓለም ሰላም ጠበቃዎች፣ የጋዜጠኞች መብቶች አስከባሪዎች፣ የዴሞክራሲ ሰብዓዊ መብቶች ተቆርቋሪዎች ነን ለሚሉትና በውጭ ሀገር የተቃዋሚዎች አፈ ቀላጤዎች በመሆን በማገልገል ላይ ለሚገኙ አንዳንድ ኃይሎች ሳይንበረከክ፣ መንግሥት የአመፅ ጥሪ የሚያቀርቡትን ኃይሎች ሀይ ሊላቸው ይገባል … ››

    ከላይ የሰፈረው ጥቅስ የተወሰደው መስከረም 12 ቀን 2004 ዓ.ም ለንባብ ከበቃው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ገፅ 3 ነው። ምንጣፍ የሚያክለው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ከርዕስ አንቀፁ ጎን «የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎች ሲጋለጡ» በሚል ርዕሥ ባሰፈረው ሰፊና ረዥም ሀተታ ይህቺኑ አውራምባ ታይምስን ጨምሮ፣ ፍትህ እና የአንድነት ፓርቲ ልሳን የሆነው «ፍኖተ ነፃነት» ጋዜጣ ላይ በተለየ መልኩ ጣቱን ቀስሯል።

    አዲስ ዘመን፣ "በተለያዩ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ዜጎች ነፃ አስተያየታቸውን የሚሰጡበት” አምድ ነው በሚል ሰበብ ያሰፈረው ረዥም ሀተታ፣ በጳጉሜ ወር 2003 ዓ.ም፣ «በአጠቃላይ ማለት ይቻላል ብዙዎቹ የግል ፕሬሶች ከርዕስ አንቀፃቸው ጀምሮ በሁሉም አዋጆቻቸው ያሰፈሩት የ2004 ዓ.ም የአመፅና የመንግስት ግልበጣ ዘመን እንዲሆን
    ጥሪ አስተላልፈዋል» ሲል ይከሳል።

    አዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደመጫኛ በረዘመውና ቅጣምባሩ በጠፋበት ረዥም ሀተታው፣ መንግሥት አውራምባ ታይምስ ጋዜጣን «ሀይ እንዲል» ያሳሰበው፣ ጋዜጣችን በባለፈው ሳምንት ዕትሟ «አስደንጋጩ አዋጅና አፈፃፀሙ» በሚል ርዕስ ለንባብ ካበቃችው ዘገባ አስረጅ ይሆነኛል በሚል ነቅሶ በማውጣት ነው።

    ዘመን «የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎች ሲጋለጡ» በሚል ርዕሥ አንድነት ፓርቲን፣ የፓርቲውን ልሳን «ፍኖተ ነፃነት» ጋዜጣ፣ እንዲሁም በማያፈናፍን ሜዳ በነፃ መንፈስ ነፃ መረጃን ለህዝብ በማቅረብ ላይ የሚገኙትን «ፍትህ» እና «አውራምባ ታይምስ»ን ለመክሰስ ይረዳው ዘንድ መነሻ ያደገው፣ መንግስት በሽብር ወንጀል ጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ያዋላቸውን የ29 ሰዎች ጉዳይ መነሻ በማድረግ ነው።

    እንደ እውነቱ ከሆነ የአዲስ ዘመን ጋዜጣ አጓጉል ክስ ለአውራምባ ታይምስ አዲስ አይደለም። አዲስ ዘመን፣ አውራምባ ታይምስ ጋዜጣን ከዚህ ቀደም እስኪታክተው ድረስ በማይጨበጥ ክስ ሲያዥጎደግድበት እንደነበረ የአደባባይ ምስጢር ነው። የጋዜጣችንን ባልደረቦች በሀገር ክህደት፣ በሻዕቢያ ተላላኪነት ወዘተ በውጭ ኃይሎች ወኪልነት ሲጠረጥር፣ ሲያስጠረጥር ነበር። አልተሳካለትም እንጂ።

    የአዲስ ዘመን ክስ ያሻውን ያህል ቢከመር፣ እኛ ግን አልደነገጥንም፤ አንደነግጥምም። ከዚያ ይልቅ መንግስታዊው አዲስ ዘመን ጋዜጣ አይረቤ ውንጀላውን እንዲያቆም ወደ ፍ/ቤት ነው የሄድነው። ፍ/ቤቱ አቤቱታችንን አይቶ ተገቢውን ውሳኔ ባይወስንም፣ ወደ ፍርድ ቤት መሄዳችን በራሱ ለሀገሪቷ ሕግ ምን ያህል ተገዢዎች እንደሆንን የሚያመላክት ነው።

    መረጃ የመቀበልና የመስጠት መብታችንን የምናከብረው እናየምናስከብረው በሕግ እና በሕግ ጥላ ሥር ብቻ ስለመሆኑ ከበቂ በላይ ማረጋገጫችንም ነው ብለን እናምናለን።አሁንም ሆነ ወደፊት ተግባራችንን የምንወጣው በሕግ ጥላ ሥር ብቻ መሆኑን መግለፅ እንወዳለን። መንግሥት ያወጣውን የፀረ-ሽብርተኝነት ሕግንም በተመለከተ ጠንቅቀን እናውቃለን። ፓርላማ በአሸባሪነት የፈረጃቸውን ድርጅቶች ጉዳይ መዘገብ አቁመናል። ምክንያቱም ለሕግ ተገዢዎች ነንና። ይሁን እንጂ የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉን በጥሬው መቃኘትና ስለሂደቱም የመዘገብና የመናገር መብት አለን።

    አዎ፤ በሽብርተኝነት ተጠረጠሩ ማለት ሽብርተኝነታቸው ተረጋገጠ ማለት አይደለም። የተጠረጠሩት ሰዎች አስኪፈረድባቸው ድረስ ቢያንስ በመርህ ደረጃ ነፃ ሰዎች ናቸው ብለን እናምናለን። የሀገሪቱም ሕግ የሚለው ይህንኑ ነው። ታዲያ አዲስ ዘመን፣ በሽብርተኝነት ስለተጠረጠሩ ሳይፈረድባቸው ስለተጠርጣሪዎቹ መዘገብን ወንጀል አድርጎ እኛ ላይ ጣቱን የሚቀስረው በምን ሎጂክ ነው?

    ቀድሞ ነገር የአዲስ ዘመን የጠርጣሪነት (Skepticism) ፍልስፍና ከየት የመጣ ነው? እኛ እስከምናውቀውና ከታሪክ እንደተረዳነው የጠርጣሪነት ፍልስፍና እጅና እግር የሌለው መሆኑን ነው። ጠርጣሪነት ለተጨበጠ፣ ለረቀቀ ዕውቀት ቦታ የማይሰጥ ያለፈበት ፍልስፍና ነው። ሌላው ቀርቶ የስሜት ህዋሳትን መረጃ እንኳ መረዳትና መገንዘብ አይፈልግም። እኛ ደግሞ እጅና እግር ለሌለው የጠርጣሪነት ፍልስፍና የምንበረግግ አይደለንም።

    ይህንን የምንለውና በእምነት የምንናገረው መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ በአዲስ ዘመን በኩል እየተሴረብን ያለውን ደባ እንዲገነዘብልን ብቻ ነው።

    ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!__

    ይህ ጽሁፍ ከአውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 186 የተወሰደ ነው!

    Views: 1153 | Added by: dani | Rating: 4.0/1
    Total comments: 0
    Name *:
    Email *:
    Code *:
    Copyright MyCorp © 2024
    Create a free website with uCoz